Asset Publisher

ዜና

የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ ላይ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና የብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታየ ደንደአ የየኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት መቋቋሚያ መመሪያ ሰነድ አቅርበዋል ።

አቶ ታዬ ባቀረቡት ፅሁፍ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም መገንባት አንገብጋቢ በመሆኑ፣ የፖሊሲ ስርዓትን ለማዘመን እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት ከተመሰረተባቸው ምክንያቶች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል ።

ተጨማሪ ያንብቡ

የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

ኅዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር ) የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ በሐይማኖት አባቶች ፀሎትና ቡራኬ ተጀምሯል ።

ተጨማሪ ያንብቡ

“ብዝኃነታችንን በተገቢው ሁኔታ ያገናዘበ ፌደራል ሥርዓት ለመገንባት ሚድያ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡”

የሰላም ሚኒስቴር ከሚዲያ አካላት እና ከዘርፉ ምሁራን ጋር ኅዳር 10 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ያዘጋጀው ውይይት የሀገራችንን ብዝኃነት ያገናዘበ ፌደራል ሥርዓት ለመገንባት የሚድያውን ሚና በሚመለከት መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቅቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥሩ አዎንታዊ አመለካከቶችና ሐሳቦችን ለሰላም እና ለኢትዮጵያዊ አንድነት እሴቶች ግንባታ እንድናውል ሚድያው አዎንታዊ ሚና መወጣት አለበት፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የሚዲያ አካላት፣ የኪነጥበብ ሰዎች፣ ደራሲያንና ሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም፣ ግጭት አስተዳደር እና ሰላም ግንባታ የሚኖራቸውን ገንቢ ሚና አስመልክቶ ከሚድያ ባለሙያዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች እና ከዘርፉ ምሁራን ጋር ኅዳር 10 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ውይይት አድረጓል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ኢትዮጵያ በጸረ-ሽብር ፋይናንስ ላይ በተካሄደው 3ኛው የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳተፈች

ህዳር 10/2015 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱአለም የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በኒው ዴሊ፣ ህንድ እየተካሄደ ባለው 3ኛው የፀረ ሽብር ፋይናንስ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል ።

ተጨማሪ ያንብቡ