ኢትዮጵያ በጸረ-ሽብር ፋይናንስ ላይ በተካሄደው 3ኛው የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳተፈች

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ኢትዮጵያ በጸረ-ሽብር ፋይናንስ ላይ በተካሄደው 3ኛው የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳተፈች

ህዳር 10/2015 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱአለም የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በኒው ዴሊ፣ ህንድ እየተካሄደ ባለው 3ኛው የፀረ ሽብር ፋይናንስ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል ። ኮንፈረንሱ ''ለሽብር የሚውል ገንዘብ የለም '' በሚል መሪ ሃሳብ ከህዳር 9 ቀን ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እየተካሄደ ይገኛል ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱአለም በኮንፈረንሱ ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኝነትን እና አለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኖችን በመዋጋት የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

አቶ ብናልፍ አክለውም በአለም አቀፍ እና በሀገር ደረጃ የሚደረጉ የሽብር ተግባራትን ለመከላከል እና ህገወጥ የፋይናንስ ግብይቶችን እና የገንዘብ ዝውውርን ለመዋጋት የመንግስት ተቋማትና የፋይናንስ መረጃ ማዕከላት ያላቸውን ሚና አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

ሽብርተኝነት ዓለም አቀፍ ስጋት መሆኑን በመረዳት ተቋማዊ ሥርዓትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የገለፁት አቶ ብናልፍ ኢትዮጵያ በገንዘብ የሚደገፍ ሽብርተኝነትን ለመከላከል ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል ።

ከኮንፈረንሱ ጎን ለጎን አቶ ብናልፍ አንዱአለም ከህንዱ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል ።

ምንጭ:- በህንድ የኢትዮጵያ ኢምባሲ