Asset Publisher

ዜና

የተጎራባች ክልሎች የመንግሥታት ግንኙነት ግጭቶችን በሰላማዊ እና በዘለቂነት ለመፍታት ሚናው የጎላ ነው ተባለ

የተጎራባች ክልሎች የመንግሥታት ግንኙነት ግጭቶችን በሰላማዊ እና በዘለቂነት ለመፍታት ሚናው የጎላ ነው ተባለ

ተጨማሪ ያንብቡ

የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሰላም ተቋም ጋር በመተባበር ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዷል

የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሰላም ተቋም ጋር በመተባበር ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዷል

 

ተጨማሪ ያንብቡ

ኢትዮጵያና ሞሮኮ በሰላም ግንባታ ጉዳዮችና የመከባበር ባህልን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን በትብብር ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሞሮኮ በሰላም ግንባታ ጉዳዮችና የመከባበር ባህልን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን በትብብር ለመስራት ተስማሙ

ተጨማሪ ያንብቡ

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር ) በእንግሊዝ ኤምባሲ የልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ከሆኑት ፓዉል ዋልትርስ (Paul Walters) ጋር ውይይት አድርገዋል፡

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ  (ዶ/ር ) በእንግሊዝ ኤምባሲ የልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ከሆኑት ፓዉል ዋልትርስ  (Paul Walters) ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

Most Viewed Assets

null የመንግስታት ግንኙነት የአስፈጻሚዎች ይፋዊ ፎረም ምስረታ ሂደት ላይ ውይይት ተካሄደ

ታህሳስ 20/2016 . (የሰላም ሚኒስቴር) " የመንግስታት ግንኙነት በኢትዮጵያ ፌደራል ስርዓት ህጋዊ ማዕቀፍ፣ አደረጃጀት፣ አሰራርና ተጨባጭ ሙከራዎች" በሚል ርዕስ ከፌደራል ተቋማት ከተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና የዲሞክራሲ ዴስክ ኋላፊ / ስመኝ ወልዴ በመንግስታት ግንኙነት ሒደት ከፌደራል ተቋማት እስከ ታችኛው መዋቅር ያለው ትብብር ለጎንዮሽ የጋራ ትብብር መነሻ መሆኑን ገልፀው ይህም ትብብር ችግሮችን በጋራ የመፍታት አቅምን ያጠናክራል ብለዋል

በሰላም ሚኒስቴር የመንግስታት ግንኙነት ዴስክ ኋላፊ አቶ ግርማ ቸሩ የምክክር መድረኩ በፌደራል መንግስትና በክልሎች መካከል መግባባትና በአጋርነት ላይ የተመሰረተ መልካም ግንኙነትና ትብብር እንዲኖር በማድረግ የፌደራል ስርዓቱ  እንዲጠናከር ማድረግ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ግርማ በኢፌዴሪ የመንግስታት ግንኙነት ስርአት ለመወሰን በሕ//ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1231/2013 የተደነገገ መሆኑን ጠቁመው ከፌደራል እስከ ክልሎች በተዋረድ ተግባራዊ እየተደረገ ያለና የጎንዮሽ ግንኙነቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትኩረት እየተሰራም ብለዋል።

አዋጁ ከመውጣቱ በፊት -መደበኛና ተጠያቂነት የጎደለው በመሆኑ የመንግስታት ግንኙነት ተግባራዊነቱን ለማረጋገጥ አንዲሁም ድጋፍና ክትትል ለማድረግ አስቸጋሪ እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተነስቷል   በተጨማሪም በየመስሪያ ቤቶች ለሚቋቋሙት አምዳዊ የትብብር ፎረሞች እንደመነሻ ሊያገለግል የሚችል ሞዴል የትብብር ቻርተር ዋና ዋና ይዘት ላይ ለተሳታፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ በአቶ ግርማ ተሰጥቷል።

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል የአማራና የቤንሻንጉል ክልልና የምስራቅ ኢትዮጵያ አምስቱ ተጎራባች ክልሎች አምዳዊ (የተዋረድ) የጋራ የትብብር መድረክ ያላቸው ሲሆን፤ የጋምቤላና የደ/ምዕ/ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እና የሲዳማ የደቡብና የኦሮሚያ ክልል የጎንዮሽ የትብብር መድረክ በመቋቋም ሒደት ላይ እንደሆኑ በቀረበው የመወያያ ሰነድ ተገልጿል።

በፌደራልና በክልሎች መካከል ጠንካራ የሆነ የጎንዮሽ የትብብር መድረክ አለመኖር፣ ህጋዊና የተጠያቂነት አሰራር አለመዘርጋት ለአፈፃፀሙ ክፍተት መሆኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሱ ሲሆን የተስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የግንኙነት ሰንሰለቱን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል