የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ ላይ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና የብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታየ ደንደአ የየኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት መቋቋሚያ መመሪያ ሰነድ አቅርበዋል ።
የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ ላይ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና የብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታየ ደንደአ የየኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት መቋቋሚያ መመሪያ ሰነድ አቅርበዋል ።
አቶ ታዬ ባቀረቡት ፅሁፍ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም መገንባት አንገብጋቢ በመሆኑ፣ የፖሊሲ ስርዓትን ለማዘመን እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት ከተመሰረተባቸው ምክንያቶች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ዋና ዋና ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች በአቶ ታየ ደንደአ የቀረቡ ሲሆን የኢትዮጵያን የሰላም ፖሊሲ ረቂቅንም አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል ።
ከዚህ ጎን ለጎን . የሰላም ሚኒስቴር የዘላቂ ሰላም ፕሮግራምና ፕሮጀክቶች ሰነድ በሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ በሆኑት በአቶ ሻንቆ ደለለኝ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል ።
በመጨረሻም ለተነሱ ሃሳቦች ከመድረኩ ማጠቃለያ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል ።