ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥሩ አዎንታዊ አመለካከቶችና ሐሳቦችን ለሰላም እና ለኢትዮጵያዊ አንድነት እሴቶች ግንባታ እንድናውል ሚድያው አዎንታዊ ሚና መወጣት አለበት፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

“ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥሩ አዎንታዊ አመለካከቶችና ሐሳቦችን ለሰላም እና ለኢትዮጵያዊ አንድነት እሴቶች ግንባታ እንድናውል ሚድያው አዎንታዊ ሚና መወጣት አለበት፡፡”

አቶ ታዬ ደንደአ

 

የሰላም ሚኒስቴር የሚዲያ አካላት፣ የኪነጥበብ ሰዎች፣ ደራሲያንና ሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም፣ ግጭት አስተዳደር እና ሰላም ግንባታ የሚኖራቸውን ገንቢ ሚና አስመልክቶ ከሚድያ ባለሙያዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች እና ከዘርፉ ምሁራን ጋር ኅዳር 10 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ውይይት አድረጓል፡፡

አዎንታዊ አመለካከቶችና ሐሳቦችን ቀርጾ ለሰላም፣ ለአንድነትና ለሀገር ግንባታ በማዋል ካለንበት ሀገራዊ የሰላም እጦት ችግር እንድንወጣ ሚድያው አዎንታዊ ሚና መወጣት እንዳለበት የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ታዬ ደንደአ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር አመላክተዋል፡፡

የሁሉንም ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፤ ከኢትዮጵያዊነት እሴቶች ጋር የተናበበ፤ ብሔረዊ ጥቅሞቻችንን አስጠብቆ ሀገራዊ መዋሃድ የሚያመጣ አስተዳደራዊ ሥርዓት ለመገንባትም ሚድያው በጎ አስተሳሰቦችን በማስተላለፍ እና የሰብዓዊነትን ክብር ከፍ በማድረግ እንዳለበት ክቡር አቶ ታዬ ደንደአ አስገንዝበዋል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክ “የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ሁኔታና ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ በኢትዮጵያ” እና “መደበኛ ያልሆኑ ተዋንያን በሰላም ግንባታው የሚኖራቸው አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖ” በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ጥናዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡