“ብዝኃነታችንን በተገቢው ሁኔታ ያገናዘበ ፌደራል ሥርዓት ለመገንባት ሚድያ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡”

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

“ብዝኃነታችንን በተገቢው ሁኔታ ያገናዘበ ፌደራል ሥርዓት ለመገንባት ሚድያ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡”

ዶ/ር ስዩም መስፍን

 

የሰላም ሚኒስቴር ከሚዲያ አካላት እና ከዘርፉ ምሁራን ጋር ኅዳር 10 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ያዘጋጀው ውይይት የሀገራችንን ብዝኃነት ያገናዘበ ፌደራል ሥርዓት ለመገንባት የሚድያውን ሚና በሚመለከት መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቅቋል፡፡

የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ስዩም መስፍን

ተገኝተው የውይይት መድረኩን መዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን “ብዝኃነታችንን በተገቢው ሁኔታ ያገናዘበ ሚዛናዊ ፌደራል ሥርዓት በሀገራችን እንዲገነባ የሚድያው ድርሻ ትልቅ ነው” ብለዋል፡፡ ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ሚዛኑን ጠብቆ እየተገነባ እንዲሄድ የሚያግባቡ መረጃዎችን ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ፣ የግንዛቤ ክፍተቶችን በመሙላት እና ሀገራዊ መረጋጋትን በመፍጠር ሂደት ሚድያ ተላላቅ ተግባራትን ያከናወነባቸውን የተለያዩ ሀገሮች ልምድ በማቅረብ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ሁለተኛው ክፍል “የብዝኃነት አያያዝ በኢትዮጵያ ፌዴራል ሥርዓት” እና “የማኅበራዊ ሚድያ በረከቶችና ተግዳሮቶች” በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ጥናዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም በነዚሁ ርዕሶች ላይ ሐሳቦቻቸውን እና አስተያየቶችን አንስተው ተወያይተዋል፡፡