የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ኅዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር ) የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ በሐይማኖት አባቶች ፀሎትና ቡራኬ ተጀምሯል ።

 

የኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔውን በንግግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱአለም የሰላም ምክር ቤቱ መቋቋም በተናጠል ስንሰራው የቆየወን የሰላም ስራ ሰብሰብ ብለን በጋራ ተመካክረን ለመስራት ያስችለናል ብለዋል ።

ሰላም የጋራ አጀንዳችን ፣የጋራ መንገዳችንና የጋራ መዳረሻችን ነው ያሉት አቶ ብናልፍ በጋራ ተመካክረን የምንፈልገውን ሰላም ለማስፈን ይህ የሰላም ምክር ቤት መመስረት ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል ።

ሠላም የእያንዳንዱን ግለሰብ ውስጣዊ ሰላም የሚጠይቅና የረጅም ጊዜ ሂደት መሆኑን ዜጎች እንዲግባቡ ፣በማህበረሰብ ደረጃ የሰላም ግንባታ ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ እና በሀገር ደረጃ ሁሉን አቀፍ ሰላም እንዲገነባ የሰላም ምክር ቤቱ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ አቶ ብናልፍ አክለው ተናግረዋል ።

በኢትዮጵያ የሰላም ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ሚኒስትሮች፣የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክልል የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት እየተካሄደ ነው ።