የሰላም ዘርፍ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ፎረም ምስረታ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 መጋቢት 2/2016 . (ሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች  በሰላም ዘርፍ ውስጥ ከሚገኙት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር የስነ- ምግባር መከታተያ ክፍሎች ጋር ''የሰላም ዘርፍ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ፎረም ምስረታ'' ተካሂዷል።

በምስረታ ፎረም ውይይቱ ላይ የሰላም ሚኒስቴር የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ አበራ ''የሰላም ሚኒስቴር  የሰላም ዘርፍ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ፎረም የአደረጃጃት እና አሰራር ማንዋል'' አቅርበዋል።

አቶ መንግስቱ የፎረሙ ዓላማ  በሰላም ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር የስነ- ምግባር መከታተያ ክፍሎች መካከል  ትስስር እና ትብብር በመፍጠር በሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ዙሪያ መረጃ እንዲለዋወጡ ማስቻል በስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ዙሪያ ጥሩ አሰራሮች እና ልምዶችን እንዲለዋወጡ ማድረግ እና ዘርፉን የሚመራው አካል በቂ መረጃ እንዲኖረው በማድረግ ተቋማዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ለማድረግ ያለመ ነው  መሆኑን አብራርተዋል።

በምስረታ ውይይቱ የተገኙ ተሳታፊዎች በቀረበው ሰነድ ላይ ሃሳብና ጥያቂያቸውን አንስተው የተወያዩ ሲሆን ከመድረክ ማጠቃለያ ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም የፎረም ምስረታው ተከናውኗል።