የተጎራባች ክልሎች የመንግሥታት ግንኙነት ግጭቶችን በሰላማዊ እና በዘለቂነት ለመፍታት ሚናው የጎላ ነው ተባለ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመተባባር በሰሜንና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የጎንዮሽ የመንግሥታት ግንኙነት መመስረቻ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
 
የፌዴሬሽን ምክክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ በሰሜንና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የጋራ የምክክር መድረክ በቀጠናው የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በሕገመንግሥቱ ማዕቀፍ በውይይትና በድርድር ለመፍታት፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ያስችላል ብለዋል፡፡ አክለውም እንዲህ ዓይነቱ የጎንዮሽ የመንግሥታት ግንኙነት ተጎራባች ማኅበረሰቦችን በመሠረተ ልማት በማስተሳሰር አንድነታቸውንና ትስስራቸውን በማጎልበት ሕብረብሔራዊ አንድነቻውን ለማጎልበት አዎንታዊ ሚና ይጫወታል በማለት ገልፀዋል፡፡
 
የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ የምክክር መድረኩ በክልሎች መካከል ወንድማማችነትንና ህብረብሔራዊነትን ለማጠናከር የሚያስችላቸውና በራሳቸው የመነጋገርና የመወያየት ልምዳቸውን የሚያዳብሩበት መሆኑን ገልፀው የጎንዮሽ የመንግስታት ግንኙነት ተቋማዊ በሆነ መልኩ ተፈጥሮ ወደ ተጨባጭ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መግባት ያስፈልጋል ብለዋል። ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም በተናጠል ማሳካት ያልቻናቸውን ጎዳዮች በጋራ ሠርተን ውጤታማ ለማድረግ የሁለቱ ተቋማት ድጋፍና ክትትል አስፈላጊ ነው ብለዋል ፡፡
የመድረክ ዋና ዓላማ የበይነ መንግሥታት ግንኙነት በኢትዮጵያ የመንግሥታት ግንኙነት አዋጅ እና አሠራር ሥርዓት መሠረት የተደገፉ እንዲሆኑ በማድረግ የፌዴራል ሥርዓቱንና የሕዝቦችን ወንድማማችነትና ሕብረብሔራዊ አንድነት ማጠናከር እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
 
 
ውጤታማ የተጎራባች ክልሎች የግንኙነት ስርዓት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ማጠናከር አስፈላጊነት የሚል ፅሁፍ ቀርቧል ውይይት ተደርጎበታል፡፡
 
በምክክር መድረኩ ላይ የተከበሩ የኢፌዲሪ ፌ/ም/ቤት ም/አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ ፣ የኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ፣ የክልል አፈ ጉባኤዎች፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት፣ የክልል ም/ር/መስተዳድሮችና ቢሮ ኃላፊዎች በምክክር መድረኩ ተሳትፈዋል::