ኢትዮጵያና ሞሮኮ በሰላም ግንባታ ጉዳዮችና የመከባበር ባህልን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን በትብብር ለመስራት ተስማሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኢትዮጵያና ሞሮኮ በሰላም ግንባታ ጉዳዮችና የመከባበር ባህልን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን በትብብር ለመስራት ተስማሙ

 የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስተር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (/) በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዢሐ አላመሐመዲ (Nezha ALAOUI M’HAMMDI) ጋር ውይይት አድርገዋል።

 

በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሀገራቱ በትብብር በሚሠሯው የጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡ ሞሮኮ እና ኢትዮጵያ የነበራቸው መልካም የዲፕሎማሲ ግንኙነት አጠናክረው የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ተግባራት በተለይም የሰላም ግንባታውን ውጤታማ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አበክረው ተወያይተዋል፡፡

 

ሚኒስቴር /ቤቱ የምክክር ባህልና ልዩነቶችን በሰላማዊ ሂደት ለመፍታት የሰላም ባህል እንዲገነባ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ሚኒስትር ዴዔታው ለአምባሳደሯ ገልፀዋል።ይህንን መልካም ጅማሮ ለማጠናከር በሁለቱ ሀገራት መካከል መከናወን ስላለባቸው  ኃላፊነቶች እና ድጋፎች ዙሪያም ተነጋግረዋል።

የሞሮኮ አምባሳደር ነዢሀ አልመሀመዲ በበኩላቸው ሞሮኮ በመቻቻልና በአብሮነት ዙሪያ ጥሩ ልምድ እንዳላት ገልፀው ኢትዮጵያም ካላት ረጅም ታሪክ በተለይ በመከባበርና በሀይማኖቶች መካከል የዳበረ መከባበር ባህልና ከሀገሪቱ ብዝሀነት አቅም በርካታ ተሞክሮ መውሰድ እንደምትፈልግም ተናግረዋል።በሀገራቱ መካከል ያለውን መቀራረብ የበለጠ ለማጠናከር የንጉስ መሀመድ ስድስተኛ ፋውንዴሽን /ቤቱን በአዲስ አበባ ለመክፈት ፍላጎት እንዳለውም አምባሳደሯ ገልፀዋል።በሀገራቱ መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማጠናከርም በትኩረት እንደሚሰሩም አምባሳደሯ ጨምረው ገልፀዋል።