የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር ) በእንግሊዝ ኤምባሲ የልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ከሆኑት ፓዉል ዋልትርስ (Paul Walters) ጋር ውይይት አድርገዋል፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

ክቡር ከይረዲን ተዘራ  (ዶ/ር )  በሰላም ሚኒስቴር በኩል  እየተሰሩ ያሉትን የሰላም ግንባታ ስራዎች አስመልክቶ ሰፊ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም  በሰላም ግንባታ ስራዎች በጋራ ለመስራት በሚኒስቴር መስረያ ቤቱ  በኩል ሰፊ ፍላጎትና ዝግጁነቱ እንዳለ  ሰፊ ገለጻ አድረዋል ፡፡

 

በእንግሊዝ ኤምባሲ የልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ፓዉል ዋልትርስ ( Paul Walters) በበኩላቸው  ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት በእንግሊዝ ኤምባሲ    በኩል  ፍላጎት እንዳላቸው  የገለጹ ሲሆን  በዚህም ከሲቪክ ማህበራት ( መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች) ጋር በመቀናጀት በሰላም ሚኒስቴር  በኩል  እየተከናወኑ ያሉ የሰላም ግንባታ ስራዎችን ለመደገፍ እና በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፈቋደኝነት  ገልጸው የሰላም ሚኒስቴር  በሰላም ግንባታ  ስራዎች ዙሪያ እያደረገ ያለውንመጠነ ሰፊ ስራዎችና ጥረቶችም  አድንቀዋል ፡፡