የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሰላም ተቋም ጋር በመተባበር ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዷል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

መጋቢት 03/2016 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሰላም ተቋም ጋር በመተባበር በሰላም ግንባታ ሂደት ሚና ካላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዷል።


በውይይት መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱና እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በንግግር ችግሮችን መፍታት የመንግስት ፅኑ አቋም መሆኑን ገልፀው የሰላም ጉዳይ የሁላችንም አስተዋፆ የሚፈልግ ለመንግስት ብቻ የሚተው አይደለም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በአንድነት ለሰላም ሊቆም ይገባል ብለዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ሰላም ተቋም ቦርድ ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ሙሉጌታ ኢተፋ (ዶ/ር)ተቋማችን በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በውይይት የመፍታት ባህልን ለማዳበር ተከታታይ የሆኑ መድረኮችን በማመቻቸት ህዝባችን በሰላም አብሮ እንዲኖር በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡ አክለውም ሰላም የእያንዳንዳችን ጉዳይና ሃላፊነት በመሆኑ ሁላችንም በጋራ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም መስራት ይኖርብናል ብለዋል ፡፡

 

የፌደራል መንግስት ተቋማት አመራሮች፣የሲቪክ ማህበራት ፣የሴቶችና ወጣቶች ማህበራት ፣ የንግድ ዘርፍ ማህበራት፣ሰላምና ፀጥታ አመራሮች  ፣ፖለቲካ ፓርቲዎች ሌሎች ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ተሳትፈዋል ፡፡