የሰላም ሚኒስቴር ከዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ የሙሀመድ ቢን ዘይድ ዩኒቨርስቲ ጋር በሰላም ግንባታ ሂደት ዙሪያ በትብብር ለመስራት በሚያስችሉት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 17/2016 .  (ሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር / ከይረዲን ተዘራ ፣የሞሃመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርስቲ ቻንስለር የሆኑትን / ኸሊፋ ሙባረክን እና የልዑካን ቡድናቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይቱም የሰላም ሚኒስቴር እና የሞሃመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርስቲ በጋራ ሊሰሯቸው በሚገቡ ተግባራት ላይ ተነጋግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታው በውይይቱ ወቅት  የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን በዝርዝር ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት እና ብዝሃ ማንነት ያለባት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ አካላትን በማስተባበ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴዔታው ሰላም በባህሪው አለም አቀፋዊ ገፅታ ያለው በመሆኑ ከተለያዩ ሀገራት የጥናትና ምርምር ተቋማት ጋር ተባብሮ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል። ለሀገራችን ወዳጅ ከሆነችው ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የትምህርት ተቋማት ጋር የሚደረገው ትብብርም ዘርፈ ብዙ ትርጉም እንዳለውም ጨምረው ገልፀዋል።

የሞሃመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርስቲ  ቻንስለር የሆኑት / ኸሊፋ ሙባረክ  በበኩላቸው ለሳቸውና ለልዑካን ቡድናቸው ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ የተለያዩ ልምዶችን እንደምትወስድና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሚያከናውናቸው የሰላም ግንባታ ተግባራት ድጋፍ ለማድረግ ዩኒቨርስቲው በትብብር እንደሚሰራም በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

 የሞሃመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርስቲ ለሰብአዊነት የተሰኘው ተቋም የሚገኘው በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የሚገኝ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሲሆን  በሀገሪቱ የሰላም ትምህርት በሁሉም የትምህርት ደረጃው እንዲሰጥ ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የመከባበር ሚኒስቴር ጋር በቅርበት የሚሰራና የሀገሪቱን የልማት ግቦች ለማሳካትና ለማህበረሰብ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያበረክቱ የላቀ ምሩቃንን ለማፍራት  የተቋቋመ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡

የመሀመድ ቢን ዘይድ ዩኒቨርስቲ ቻንስለር በሰላም ግንባታ ዙሪያ ከሚኒስቴር /ቤቱጋ በትብብር ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።