ከግል ከፍተኛ ትምህርት፣ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማኅበር አባላት ጋር ውይይት ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 14/2016 . (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ማኒስትር ዴዔታ ክቡር / ከይረዲን ተዘራ በኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር አባላት ጋር ተወያይተዋል።

 / ከይረዲን ተዘራ የዛሬው የውይይት መድረክ ዓላማ የትውውቅ እና የግል ከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በሰላም ግንባታና በሀገራዊ ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና እንዲወጡ ተቀራርቦ ለመስራት ያለ ነው ብለዋል።

የግል ከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በውስጣቸው  የያዙት የህብረተሰብ ክፍል ቀላል እንዳለመሆኑ መጠን በሀገር ግንባታና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ተቀራርቦና ተደጋግፎ መስራት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር ኬረዲን አክለውም የሰላም ሚኒስቴር የተቋቋመበትን ዓላማ እና እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን  በውይይቱ ላይ ለተገኙ አመራሮች በዝርዝር ያስረዱት ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመማር ማስተማሩ ባሻገር በሀገራዊ ማንነት፣ዕሴትና  ጥቅም ላይ እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ከግል፣ ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የመጡ አመራሮች በበኩላቸው እኛ የአንድ ሀገር ዜጋ እንደመሆናችን መጠን ስለ ሰላም መስራት እራስ ላይ መስራት እንደሆነ እናምናለን ለዚህም ዝግጁ ነን ያሉ ሲሆን ለዚህ ሥራ በመጠራታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡