‹‹አድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ›› በሚል መሪ ሃሳብ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 9/2016 . (ሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር  ‹‹አድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት  ግንባታ››   በሚል መሪ ሃሳብ  በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰላምና ሀገር ግንባታ ፎረም ለሚከናወን ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ ማስጀመሪያ መርሀ ግብርን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር / ከይረዲን ተዘራ እና የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ናቸው፡፡

ክቡር / ከይረዲን ተዘራ በመግለጫቸው የአድዋን ድል ለድል ያበቃው የመላው ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ ነው ያሉ ሲሆን ለዘላቂ ሰላማችን መስፈን የእያንዳንዳችን ድርሻ ወሳኝነት አለው ብለዋል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 21 ቀን 2016 . ‹‹አድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት  ግንባታ››   በሚል መሪ ሃሳብ  በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰላምና ሀገር ግንባታ ፎረም የሚካሄደው  ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ ተማሪዎች እና የዩኒቨርስቲ ማህበረሰቦች በሀገራዊ ዕሴቶቻችን፣በሀገራዊ ማንነቶቻችን እና በብሔራዊ ጥቅሞቻችን ላይ ውይይትና ምክክር ያደርጋሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አባቶቻችን ጠንካራ ሀገራዊ እሴቶችን ፣ሀገራዊ ማንነቶችን እና ሀገራዊ ጥቅሞቻቸውን አስቀድመው ነው አድዋን ድል ያደረጉት ያሉት ክቡር / ከይረዲን  ለዚህ ነው ይህን ንቅናቄ አድዋን ተምሳሌት አድርገን የተነሳነው ብለዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሥራ ውጤታማ የሚሆነው ሰላም ሲኖር ነው ያሉ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትንሿ ኢትዮጵያ እንደመሆናቸው መጠን በሰላምና በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ መስራት ስላለባቸው ነው የዚህ ንቅናቄ ባለቤት የሆኑት ብለዋል፡፡

ከአድዋ ድል የምንማረው ትልቁን ስዕል ማየት ነው ያሉት ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የአድዋን መንፈስ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማምጣት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡