ለተቋሙ የተሰጡ ተግባርና ሀላፊነቶች እና የሚጠበቁ ውጤቶች እንዲሁም በሰላም ግንባታ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 26/2016 . (ሰላም ሚኒስቴር ) የሰላም ሚኒስቴር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራርና አባላት ለተቋሙ የተሰጡ ተግባርና ሀላፊነቶች እና የሚጠበቁ ውጤቶች እንዲሁም በሰላም ግንባታ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር / ካይረዲን ተዘራ የውይይቱን ዓለማ ሲገልጹ ቋሚ ኮሚቴው በሀገራዊ ሰላም ግንባታ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ እና ለተቋሙ በአዋጅ የተሰጡት ተግባርና ሀላፊነት ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ  ለተቋሙ ውጤታማነት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ሀገራዊ መግባባትና አንድነትን በማሳደግ ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም መገንባት ተልዕኮ የተሰጠው በመሆኑ የሀገራችን ዘርፈ ብዙና ውስብስብ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ ስራዎችን እየሰራም እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን ወጣቶች የሀገር ፍቅርን እንዲያዳብሩና በሂደቱም ህብረብሄራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን እንዲያጠናክሩ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ቀርጾ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

  ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የሰላም ግንባታ፣ ብሔራዊ መግባባት፣ በሁሉም አካባቢዎች ግጭት እንዳይፈጠር የማድረግ ስራ የሁሉም አካል የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ አገራዊ አጀንዳ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ በመስራት ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ይኖርብናልም ብለዋል፡፡

ለቋሚ ኮሚቴው "ሀገራዊ ሰላም ግንባታ ጥረት ውስጥ የፓርላማው ሚና" በሚል ርዕስ ጹሁፍ ጂይላን ወልይ ሁሴን (ፕሮፊሰር) ያቀረቡ ሲሆን ለተቋሙ በአዋጅ የተሰጡ ተግባርና ሀላፊነቶች እና የሚጠበቁ የላቁ ውጤቶችን የሚለውን ያቀረቡት ደግሞ በሰላም ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ አዱኛ በቀለ ሲሆኑ ተቋሙ በዋነኝነት አወንታዊ ሰላምን ማስጠበቅና ማስከበር፣ ብሄራዊ መግባባት እና ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን መገንባት፣ የፌዴራል ስርዓቱን ማጠናከርና የግንኙነት ማዕከል ማድረግ እንዲሁም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ትኩረት ሰጥቶ  የተሰጠውን ተልዕኮና ኃላፊነት ውጤታማ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡