ሀገር አቀፍ የሰላም ፎረሞች ጥምረት ምስረታ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 23/2016. (የሰላም ሚኒስቴር ) የሰላም ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የሰላም ፎረሞች ጥምረት ምስረታ አካሄዷል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ ወንድወሰን መኮንን የዛሬው መድረክ ዓላማ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጠንካራ ሀገር አቀፍ የሰላም ፎረሞች ጥምረት በመመስረት  ለሰላም ግንባታ ስራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡ አክለውም ጥምረቱ የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ስራችን ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች እና የስኮላርሺፕ ዴስክ ኃላፊ / ኢዶሳ ተርፋሳ ሰላም ሚኒስቴር እንደ ተቋም ከተቋቋመ በኋላ ከተቋማችን ጋር የሰላም ግንባታ ስራዎችን በጋራ ለመስራት የመግባበቢያ ሰነድ ስምምነት በመፈራረም ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው በሁለቱ ተቋማት ጥምረት አማካኝነት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋቋሙት የሰላም ፎረሞች ተግባብተው በመስራታቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የነበረውን የሰላም ዕጦት መቅረፍ ተችሏል ብለዋል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ መሪ ስራ አስፈፃሚ / አወቀ አጥናፉ  በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የሰላም ፎረሞች ሀገር አቀፍ የሰላም ፎረሞች ጥምረት እንዲቋቋም  ጥያቄ ያቀርብ እንደነበር ገልፀው በዛሬው ዕለት ሀገር አቀፍ የሰላም ፎረም ልታስፈፅሙ ኋላፊነት የተሰጣቹ ተማሪዎች  በዮኒቨርሲቲ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመነጋገር በሰላም ለመፍታት ትልቅ ሀላፊነት አለባችሁ  በተቋማችን በኩልም አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ብለዋል።

የሰላም ፎረም ማስፈፀሚያ ማንዋል እና የሰላም ፎረሞች ጥምረት ለሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት መወያያ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቻዋል ፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የከፍተኛ ትምህት ተቋማት የሰላም ፎረም ሰብሳቢዎች በመድረኩ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡