የሰላም ግንባታ ሥራዎች ያመጡትን ውጤቶች ለማወቅ በተደረገው ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 21 ቀን 2016 . (የሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ግንባታ ሥራዎች ያመጡትን ውጤቶች ለማወቅ በዘርፉ ምሁራን በተደረጉ የጥናት ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መርሐ ግብር ተደርጓል፡፡

መርሐ ግብሩ የሰላም ሚኒስቴር ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ሰላምን ለማምጣት የተገበራቸውን ተግባራት ውጤታማነታቸውን ለማወቅ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ባደረገው የጥናት ግኝት ላይ መሠረት ያደረገ ምርመራ በማድረግ ለቀጣይ የሰላም ግንባታ ሥራዎች ተጨማሪ ግብዓት የማሳበሰብ ዓላማ ያለው ነው፡፡

  መድረኩን በንግግር የከፈቱት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነሚኒስቴሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ለሰላም የሠራቸውን ሥራዎች በጥናት በመቃኘት የነበሩትን ችግሮች ፈትቶ፤ ውጤታማ አፈጻፀሞችን በበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም ወደፊት የሚሠሩ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ለማድረግ ታስቦ የተጠና ነው፡፡ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

 

የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኸይረዲን ተዘራ (/) የሰላም ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን አንድ ወገን ብቻ የሚሠራው ሳይሆን የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ ስለሆነ ለሰላም ግንባታ የሚሠሩ ሥራዎች ውጤታማ ሆነው በቀጣይ በሀገራችን አዎንታዊ ሰላም እንዲሰፍን በትብብር መሥራት መቻል አለብንሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ቀጣይ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የመስኩ ተመራማሪዎችን በስፋት ያሳተፈ የጥናት ሥራዎችን ለመሥራት እና ባለ ድርሻ አካለትን ሚና ያካተተ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለማከናወን መታቀዱን የሰላም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈጻሚ / አወቀ አጥናፉ ገልጸዋል፡፡ ለሥራው ስኬታማነት አስተዋጽዖ ላደረጉትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡