ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ ግንኙነትና የሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ስልጠና ተሰጠ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

(መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም)

ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከGIZ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአዳማ ከተማ ባዘጋጀዉ ስልጠና ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ ግንኙነትና የሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል ።

ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰላም ግንባታ ጀነራል ዳይሪክተር ዶ/ር ራህዋ ሙሴ በአገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተነሱ ያሉ ግጭቶች መነሻቸዉ ከአመለካከትና ከአስተሳሰብ ተቃርኖ መሆኑን ገልፀዉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ችግሩን ለመፍታት በሰዉ ልጅ የአዕምሮ ልማት ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎች በተለያዩ ጊዚያት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል ።

ዶ/ር ራህዋ አክለዉም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ ግንኙነትና የሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ቀድሞ የነበሩንን መልካም ዕሴቶቻችን በማጎልበት ፣ የሰከነ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊና መስተጋብሮችን በማጠናከር ረገድ ሚናቸዉ ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል ።

በሰላም ግንባታና ላይ ስልጠና የሰጡት ዶ/ር አምባየ ኦጋቶ ስለ ግጭትና የሰላም ምንነት ፣ስለ ሰላም ግንባታ መርሆዎችና መሰል ሃሳቦችን አንስተዉ ስልጠና ሰጥተዋል ።

ስልጠናዉ በሰላም ግንባታ ፣ በግጭት መከላከልና አፈታት ፣በብሄራዊ መግባባት ላይ ትኩረቱን አድርጓል ።

የስልጠናዉ ተሳታፊዎችም የተለያዩ ሃሳቦችን አንስተዉ ተወያይተዋል ።