በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች እና በጋምቤላ ክልል የመንግሥታት ግንኙነት ፎረም ምሥረታ ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 16/2016 . (የሰላም ሚኒስቴር) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት እና የጋምቤላ ክልል መንግሥታት የሰላምና ልማት የጋራ ፎረም ምሥረታ ተደርጓል፡፡ ፎረሙ የክልሎቹን ግንኙነትን በማጠናከር በትብብር፣ በአጋርነትና በቅንጅት በመሥራት በጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለምየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እና የጋምቤላ ክልል የሰላምን አስፈላጊነት ለሕዝቡ በጥልቅ አስገንዝበው ወደ ሰላም መንገድ እንዲመለሱ ያደረጉ በመሆናቸው እና ግጭት ቀስቃሽ ሴራዎችን ያከሸፉ፣ እንዲሁም በማኅበረሰቦች ባህላዊ የእርቅ ሥርዓቶች እንዲዘጉ በማድረግ፤ ሰላምን ለማስፈን የሠሩት ሥራ ለሌሎች ክልሎችም ተምሳሌት የሚሆን ነውብለዋል፡፡ ለዚህም ለክልሎቹ ሕዝብና አመራር ምስጋና አቅርበዋል፡፡ዛሬ በምናደርገው የፎረም ምሥረታ በክልሎቹ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ወደ ኋላ እንዳይመለስ ዘላቂ ለማድረግ እና በቀጣይም ለሚሠሩ የሰላም ግንባታ ሥራዎች ልምድ አዳብረን ከሁለቱ ክልሎች ባሻገርም በመሥራት በመላው ሀገሪቱ ሰላምን ለማስፈን ቃል የምንገባበት ሊሆን ይገባልሲሉም ክቡር አቶ ብናልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ-መስተዳድር / ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾሰላምና ልማት የማይነጣጠሉ የመንግሥት እና የማኅበረሰብ ትብብር ውጤት ስለሆኑ ሰላምን ለማጽናት የማኅህበረሰቦችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር በማሳለጥ የልማት አቅሞችን በተጨባጭ ማሳደግ ይጠበቅብናልብለው ይህን ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ዓይነተኛ ሚና ለመጫወት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት እና የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡ የሁለቱ ክልል ሕዝቦች በተመሳሳይ የመልክዓ-ምድር አቀማመጥ፣ የአየር ፀባይ እንዲሁም በርካታ የጋራ እሴቶችን በሚጋሩ ማኅበረሰቦች የተገነቡ የጋራ ሥነልቦና ያላቸው ኢትዮጵያዊያን እንደመሆናቸው ለጋራ ሀገራቸው ሰላም ጠንክረው እንደሚሠሩም ገልጸዋል፡፡

 

                                                                                                       

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ክቡር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የተደረገው የፎረም ምሥረታ በሁለቱ አጎራባች ክልሎች በተዋረድ በሚገኙ አስተዳደራዊ መዋቅሮች የሚከሰቱ የወሰን ጉዳዮችን እና ለጋራ ሰላማችን እንቅፋት የሚሆኑ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ፈትተን፣ ቀጠናውን ወደ አስተማማኝ  ሰላም ለማሸጋገር  የጋራ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮችን በበለጠ ለማጎልበት የሚያስችል ፎረም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ  አመራሮች በወሰን አካባቢ የሚነሱ ወሰን ተሸጋሪ ወንጀሎችን ሕገወጥ የመዕድን ቁፋሮ እና ሌሎች ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል በቅንጅት የሚሠሩበትን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ፎረም መሆኑን አመላክተው ለተግባራዊነቱ ሁሉም ቁርጠኛ እንዲሆን አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ሥርዓት የመንግሥታት ግንኙነትን አስመልክቶ ለሰላምና የልማት ፎረም ምሥረታው ውይይት የሚሆን ጽሑፍ በሰላም ሚኒስቴር የመንግሥታት ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ በሆኑ አቶ ግርማ ቸሩ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡