በሀገር ግንባታ መሰረታውያን ላይ ትኩረት ያደረገ ከሀይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ምክክር ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 16 ቀን 2016 . (ሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር  "የሀገር ግንባታ መሰረታውያን" በሚል ርዕስ ከሀይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር  ምክክር አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሰላም ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መብራቱ ካሳ  የዛሬው የውይይት መድረክ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን በማጎልበት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ መደላድል ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል ፡፡

 

 እንደ ሀገር እና እንደ ዜጋ የጋራ ታሪኮችና የወል ህልሞች፣ የጋራ መገለጫዎችና የጋራ ስጋቶች፣ የጋራ ጥቅሞችና የጋራ እሴቶች፣ የጋራ ባህሎች ወጎችና ትውፊቶች፣ የጋራ ምስል፣ የጋራ ስሜትና የጋራ አረዳድ ሊኖሩን ይገባልም ብለዋል፡፡

ሀገር ግንባታ ስንልም በእያንዳንዱ ዜጋ አዕምሮ እና ልብ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ማንነት የመቅረጽ ተግባር ነው፡፡ይህ ተግባርም ቸል ሳይባል የሁል ጊዜ ተግባር ተደርጎ ሁሉም በተሰማራበት የሙያ መስክ ሊገነባው የሚገባ ጉዳይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

አቶ መብራቱ ሀገራዊ መግባባትን ለማጎልበት ሀገራዊ ማንነትን፣ እሴቶችን እና ሀገራዊ ጥቅሞችን እንደዜጋ የጋራ ማድረግ የሚጠይቅ ሲሆን የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እነዚህን የሀገር ግንባታ መሰረታውያን ማወቅና ለህብረተሰቡ ማስረጽ ትልቅ ሃላፊነት መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

 

በውይይት መድረኩ የሀገር ግንባታ መሰረታውያን ሀገራዊ ማንነት፣እሴትና ጥቅም ግንባታ የሚል ጹሁፍ በሰላም ሚኒስቴር የብሄራዊ መግባባት ዴስክ ሀላፊ በሆኑት አቶ ገዛኸኝ ጥላሁን የቀረበ ሲሆን ሀገራዊ እሴቶች ግንባታ የሚል ጹሁፍ የማህበራዊ ሀብት ግንባታ ዴስክ ሀላፊ በሆኑት በአቶ ሀይለ መስቀል ፀጋዬ ቀርቦ ውይይት ተካሄዷል፡፡

 

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና የብሄራዊ መግባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ፍሬሰንበት /ተንሳይ በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ለሰላም ሚኒስቴር ብቻ የሚሰጥ ሳይሆን ሁሉም ማህበረሰብ በተለይም የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች  ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም ድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡