18ኛው የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን "ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት "በሚል መሪ ቃል ተከበረ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ህዳር 27/2016 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ከፋይናንስና ደህንነት አገልግሎትና ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ጋር በጋራ በመሆን 18ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አክብሯል ፡፡

 

በፕሮግራሙ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ታዬ ደንደአ እኛ ኢትዮጵያዊያን የተለያየ ቋንቋና ባህል ያለን ነን ይህን ልዩነታችንን ማክበር ማድነቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ክቡር ሚኒስተር ዴኤታው አክለውም ሰላማችንንና ጥቅሞቻችንን ማረጋገጥ የምንችለው አንድነታችንንና ብዝሃነታችንን ማጠናከር ስንችል ነው በማለት ገልፀዋል፡፡

 

የአራቱም ተቋማት አመራርና ሰራተኞች በፕሮግራሙ የተገኙ ሲሆን በዓሉን የሚመለከት ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡