ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) የግሎባል ፒስ ፋውንዴሽን የአፍሪካ ተወካይ የሆኑትን ካንሲ ቺንካ (ዶ/ር) በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) የግሎባል ፒስ ፋውንዴሽን የአፍሪካ ተወካይ የሆኑትን ካንሲ ቺንካ (ዶ/ር) በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት እንዳሉት የሰላም ሚኒስቴር እያከናወናቸው ያሉትን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት እና መሰረታዊ የሀገር መንግስት ግንባታ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የንቅናቄ ስራዎችን ገልፀውላቸዋል።

 

 

የሰላም ሚኒስቴር ለቀጣናዊ ሰላም እና ትስስር መሰረት የሚሆኑ የተለያዩ አህጉራዊ እና ዓለማቀፋዊ ኮንፈረንሶችን ማድረጉን የገለፁት ሚኒስትር ዴዔታው አፍሪካዊያን ለጋራ ሰላም እና እድገት በትብበር ከሰሩ ብዙ ለውጦችን ማስመዝገብ ይችላሉ ብለዋል፡፡

ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) አክለውም የሰላም ሚኒስቴር የዘላቂ ሰላም ስራዎችን እና የብሔራዊ መግባባት ተግባራትን ለማጎልበት በሰላም ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን የዛሬው ውይይትም የዚህ አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡

የግሎባል ፒስ ፋውንዴሽን የአፍሪካ ተወካይ ካንሲ ቺንካ (ዶ/ር) በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ ለአፍሪካዊያን ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት ያሉ ሲሆን በተለይ ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚያጋጥማትን ችግር የምትፈታበት መንገድ ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት ትምህርት የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም በዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት ዙሪያ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡