ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳይ አስተባባሪ ልዑክ ጋር ውይይት አደረጉ
ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳይ አስተባባሪ ልዑክ ጋር ውይይት አደረጉ
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ግጭቶችን ለመከላከል እና ሀገራዊ የሰላም ግንባታን ለማሳድግ በትብብር መሥራት በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳይ አስተባባሪ ልዑክ ጋር ውይይት አደረጉ::
ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፤ ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳይ አስተባባሪ ልዑክ ጋር ግጭቶችን ለመከላከልና የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የህዝቦችን ትስስርና አንድነት በሚያጠናክር እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን በሚያፀና መልኩ ተፈናቃዮችን ወደ ቀድሞ ቀያቸው በመመለስ እና የተረጋጋ ሕይወትን እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየሠራ ያለውን ሥራ አስመልክተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ግጭቶች እንዳይፈጠሩ መከላከልና ሲፈጠሩም በሰላማዊ ውይይት መፍታት ሰፊ ጥረት የሚጠይቅ እና ልዩ ልዩ ባህሪያት ያለው በመሆኑ ከተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና አጋር አካላት ጋር በትብብር መሥራትን የሚጠይቅ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳዮች አስተባባሪ ዶ/ር ራሚስ አልካብሮቭ በኢትዮጵያ ግጭትን ለመከላከልና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት እየተሠሩ ያሉትን ሥራዎች አድንቀው እየተከናወኑ ያሉትን ግጭት የመከላከልና የሰላም ግንባታ ሥራዎችን እንደሚደግፉ ቃል ገብተዋል፡፡