ሀገራዊ ችግሮቻችንን በዘላቂነት ለመፍታተ የሴቶችን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ተባለ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

(ታህሳስ 22 ቀን 2012 ዓ.ም)

ይህ የተባለዉ የሰላም ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክሬት ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ከታህሳስ 21 እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በስርዓተ ፆታ ላይ ያተኮረ ስልጠና በሰጠበት ወቅት ነዉ ።

በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማኔጅመንትና ድጋፍ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ጀነራል አቶ መብራቱ ካሳ ሴቶችና ህፃናት በሀገራችን ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የህዝብ ቁጥር የሚይዙ በመሆናቸው እነሱን ያላሳተፈ ልማትና ዴሞክራሲ ግቡን አይመታም ብለዋል፡፡

አቶ መብራቱ አክለውም ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሴቶችና ወጣቶች አስተዋፆ ከፍተኛ በመሆኑን መረደዳትና ለተግባራዊነቱም መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ።

አያይዘውም የስልጠናው ዓላማ የሰላም ሚኒስቴር በሚያከናውናቸው የስራ እንቅስቃሴዎች እና በሚያዘጋጁት እቅድ ላይ ሴቶችና ወጣቶችን አካተው እንዲሰሩ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡

በስልጠናዉ ላይ የስርዓተ ፆታ ማካተቻና የስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጪ ክትትልና ግምገማ ስርዓት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ።