የፖሊስ ተቋማት አገልግሎትን ለማዘመን የተካሄደው የዳሰሳ ጥናት ፖሊስ በህዝብ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተገለፀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር ከፌዴራልና ከክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ከአዲስ አበባና ከክልል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የኢትዮጵያ ፖሊስ ተቋማት አገልግሎትን ለማዘመንና ፕሮፌሽናል ለማድረግ በተዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት ግኝትና ረቂቅ ዶክትሪን ላይ ውይይት አካሂዷል ፡፡

  በውይይት መድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደተናገሩት የዳሰሳ ጥናት ዶክተሪኑ የፖሊስ ተቋማትን አገልግሎት ከማዘመን ባሻገር በፖሊስ ተቋማት መካከል ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር የሚችልና ፖሊስ በህብረተሰቡ ያለውን ተቀባይነትን ማጠናከር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ይህንን ዶክትሪን አጠናቆ በተግባር ላይ እንዲውል ለማድረግ ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር መድረኮችን በመፍጠር ለጥናቱ ግብዓቶችን የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ እንደሆነ የገለፁት ክብርት ሚኒስትሯ በቀጣይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመገናኘት ግብዓቶችን የማሰባሰቡ ስራ ቀጣይነት እንዳለው አክለው ገልፀዋል፡

 

የፖሊስ ተቋማትንና የአገልግሎት አሰጣጥን ከአገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች እንዲሁም አካባቢያዊና ዓለማቀፍ ለውጦች ጋር ተጣጥመው ሊሄዱ የሚችሉ በማድረግ ፕሮፌሽናልና ዘመናዊ የሆነ የፖሊስ ተቋም በመንንባት ሰላምና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ የጥናት ዋና ዓላማ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ በህብረተሰቡ ሆነ በፖሊስ ላይ ያሉ ችግሮችን መፍታት የሚያስችልና በፌዴራልና ክልልሎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክርና የአሰራር ሂደቱም ወጥነት ባለው መልኩ ማስቀጠል እንደሚያስችል የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡