የሰላም ሚኒስቴር አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ስተርሊነግ ፋውንዴሽን  ጋር በሰላም ግንባታ ዙሪያ ውይይት አካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ስተርሊንግ ፋውንዴሽን (Sterling Foundation)  ጋር በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል ፡፡ 

የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍን በመወከል ማብራሪያ የሰጡት  የሰላም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ  ዶ/ር አወቀ አጥናፉ ስተርሊንግ ፋውንዴሽን ከዚህ በፊት በሰጠው ድጋፍ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ለተደረጉ የሰላም ግንባታ ስራዎች  በጎ አስተዋጽኦ ያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ 

ስተርሊንግ ፋውንዴሽንን ወክለው የተገኙት የልዑኩ አባላትም የሰላም ሚኒስቴር አወንታዊ  ሰላምን ለማረጋገጥ እየሰራ ያለውን እንቅስቃሴ ያደነቁ ሲሆን ተጨማሪ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ሰፋፊ ስራዎችን ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡