ሰላም : ፍቅር : አንድነት : ኢትዮጵያን ያሻግራል!

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰላም : ፍቅር : አንድነት : ኢትዮጵያን ያሻግራል!

ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በሁሉም ሀገሪቱ ክፍል አዲስ አበባን ጨምሮ በሰላሳ ሶስት የተመረጡ ከተሞች "ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው አገር አቀፍ ሩጫ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሰላም ያለንን ቁርጠኝነት ለመላው አለም አሳይተናል።

ሰላም ለመሆን ብቸኛው እና አማራጭ የሌለው መንገዳችን ሰላም እራሱ በመሆኑ፤ ለሰላም የማንከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ በተግባር ላሳያችሁ ድንቅ ኢትዮጵያን በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ሁሉም የሀገራችን ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ለሀገራችን ሰላም ላሳያችሁት ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እጅግ አደንቃለሁ።

ሰላሟ የበዛና የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ዛሬም ነገም በትጋት እና በጋራ እንሰራለን።

ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ!!!

 

ሰኔ 30/2016.

ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም

የኢፌዴሪ የሰላም ሚንስቴር ሚኒስትር