ዛሬ ህዳር 3/2015:- የሰላም ሚኒስቴር በፌደራሊዝምና የመንግስታት ግንኙነት ላይ ስልጠናና ምክክር ከክልሎችና ከከተማ መስተዳድሮች ከተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በማካሄድ ላይ ይገኛል።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ዛሬ ህዳር 3/2015:- የሰላም ሚኒስቴር በፌደራሊዝምና የመንግስታት ግንኙነት ላይ ስልጠናና ምክክር ከክልሎችና ከከተማ መስተዳድሮች ከተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የፌደራሊዝም ፅንሰ ሀሳቦችና መገለጫ ባህሪያት እንዲሁም አስፈላጊነት፤ ፌደራሊዝም ግጭትን ለመቅረፍና ለመፍታት ያለው ጥቅምና የመንግስታት ግንኙነት አዋጅ በምሁራን በመዳሰስ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ሥርዓት ዘላቂ ሰላም ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ልማት በማምጣት አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚተገበር እንደሆነ ተገልጿል።

የክልሎችንና የመንግስት መንግስት ግንኙነት በማሳደግ ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን መቅረፍ የጋራ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ለልማት የሚውሉ እምቅ አቅሞችን በጋራ መጠቀም እንደሚገባ በስልጠናው ላይ ተጠቅሷል።

የመንግስታት ግንኙነት የሕገ መንግሥቱን የበላይነት ማክበር ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል የተባለ ሲሆን ግልፅ አሳታፊና በትብብርና የጋራ መግባባትን ለመፍጠር የሚተገበር እንደሆነ ተገልጿል።