ማህበራዊ ሀብቶች አብሮ በመኖር ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን  ከመፍታት  አንፃር ያላቸው ሚና አይተኬ ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር መካከል በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር እና በህብረተሰቡ መካከል የሰላም፣የመከባበርና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር የግንዛቤና ንቅናቄ ስልቶችን ቀይሶ መስራት ነው።

ይህ ሀገራዊ ተልዕኮ ይሳካ ዘንድ እንደ ሀገር በማህበረሰቡ ውስጥ ለዘመናት የዳበሩና የተከማቹ ማህበራዊ ሀብቶች እና ዕሴቶችን ለሰላም ግንባታ እና ለሀገር ግንባታ ማዋል ደግሞ ወቅቱ የሚጠይቀው የቤት ሥራ ነው፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የማህበራዊ ሀብት ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ ኃይለመስቀል ፀጋየ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት የሰላም ሚኒስቴር ያሉንን ማህበራዊ ሀብቶች ለሰላም እና ለሀገር ግንባታ ለማዋል ትልልቅ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

እንደ ሀገር በማህበረሰቡ ውስጥ ለዘመናት የዳበሩና የተከማቹ ማህበራዊ ሀብቶች እና ማህበራዊ ዕሴቶች አሉን ያሉት አቶ ኃይለ መስቀል የሰላም ሚኒስቴር በህግ ከተሰጡት ተልዕኮዎች አንፃር እነዚህ ማህበራዊ ሀብቶች ሰላምን ለመገንባትና ሀገርን ለመገንባት ያላቸውን ሚና በመረዳት ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ማህበራዊ ሀብቶች ካላቸው ሀገራ ፋይዳዎች መካከል የመጀመሪያው ማህበረሰብን ማስተሳሰር፣ ማዋህድ፣ ማግባባት እና አብሮ በመኖር ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባበቶችንና ግጭቶችን  መፍታት መሆኑን ገልፀው ማህበራዊ ሀብቶች ከሌሎች የግጭት መፍቻ ዘዴዎች አንፃር ሲታይ  ዋጋቸው አይተኬ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ተቋም ሰላም ግንባታን ስናስብ አንዱ የሰላም መገንቢያ ምሰሶ በማህበረሰቡ ውስጥ ለዘመናት የቆዩ የግጭት መፍቻ ስልቶችና የማህበራዊ ግንኙነቶች ናቸው ያሉት ኃላፊው እነዚህን ማህበራዊ ሀብቶች ለመጠበቅ እና በተገቢው መንገድ ለማዋል በጥናት ላይ የተመሰረቱ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል፡፡  ይቀጥላል

                          ሰላም ለኢትዮጵያ!