በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ጎፍለላ እና አሹቴ ቀበሌዎች በደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ የተደረገው በሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የተመራው የፌደራል፣ የክልሎች እና የዞን አመራሮችን ያካተተ ልዑክ ችግሩ የደረሰበት ቦታ ላይ በመገኘት ነው፡፡

ክቡር አቶ ብናልፍ “እዚህ ድረስ የመጣነው በገጠማችሁ ችግር ከጎናችሁ መሆናችንን ለመግለጽ እንዲሁም ለተፈጠረው ችግር እጅ እንዳትሰጡ፤ ይልቁንም ችግሩን በጥናት ላይ ተመሥርቶ ወደ ዕድል ለመቀየር እና ዘላቂ መፍትሔ በማበጀት ለልማት ማዋል በሚቻልበት ሁኔታ መንግሥት እና ሕዝብ ከጎናችሁ መሆኑን አውቃችሁ እንድትጠነክሩ ለማድረግ ነው” ብለዋል፡፡

ተጎጂዎች አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ከወረዳ እስከ ፌደራል ያሉ የመንግሥት መዋቅሮችና የተለያዩ አካላት ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ድጋፉ እንዲቀጥልና ችግሩ ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል፡፡