የሰላም ሚኒስቴር ከአማራ ክልል የሰላም ካውንስል አመራሮች ጋር ውይይት አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት የተቋቋመውን የሰላም ካውንስል አመራሮች ተቀብለው አነጋግረዋል።

የሰላም ካውንስሉ ሰብሰቢ አቶ ያየህ ይራድ በለጠ ካውንስሉ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ በመንግስትና በፋኖ ሃይሎች መካከል ድርድር እንዲያደርጉ የማቀራረብ ስራ ለመስራት "ማመቻቸት" ነው ሚናው ብለዋል።

አያይዘውም የሰላም ካውንስሉ በህዝባችን ነፃ ፈቃድና ፍላጎት የተቋቋመና ግጭቱ ከፍተኛ ተጽዕኖ በህዝባችን ላይ እያሳደረ ስለሆነ በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች የሚታዩ ግጭቶች በዘላቂነት በድርድርና በውይይት ተፈተው የክልሉ ሰላም ወደ ነበረበት ሁኔታ እንዲመለስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ካውንስሉ የተቋቋመለት ዓላማ እንዲሳካ ሁለቱም ወገኖች የየድርሻቸውን አዎንታዊ ሚና ሊያበረክቱ ይገባል ብለው የክልሉም ሆነ የፌዴራል መንግስት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ዕገዛ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በክልሉ ግጭት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ መንግስት ችግሮች በንግግርና በውይይት እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አንስተው፣

መንግስት ሁለቱንም ወገን አሸናፊ የሚያደርገውና ብቸኛው አማራጭ መፍትሄ በሰለጠነ መንገድ ተወያይቶ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት እንደሆነ በጽኑ ስለሚያምን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል ብለዋል። አሁንም መንግስት በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በንግግር ችግሮች እንዲፈቱና ግጭቶች እንዲቆሙ ለማድረግ በሩ ክፍት መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል።

በተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን ለመፍታትና የታጠቁ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ በንግግርና በውይይት ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ መንግሥት ባሳየው ቁርጠኝነት በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የነበሩ ግጭቶች መቆማቸውንና ሰላም መፈጠሩን ለአብነት ማንሳት ይቻላል ብለው፣ የሰላም ሚኒስቴርም ለሰላም ከሚሰራ የትኛውም አካል ጋር አብሮ በትብብርና በቅንጅት ለመስራትና ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።