የሰላም ግንባታ ስርዓተ- ፆታ ማካተቻ ስትራቴጂ ላይ ውይይት ተካሄደ
የሰላም ግንባታ ስርዓተ- ፆታ ማካተቻ ስትራቴጂ ላይ ውይይት ተካሄደ
ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከዩኤን ውሜን (UN-Women) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው የሰላም ግንባታ ስርዓተ- ፆታ ማካተቻ ስትራቴጂ ላይ ውይይት ተካሄደ።
በሰላም ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴዔታ ማዕረግ የሚኒስትር አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ የስርዓተ-ፆታ ህግ ዓለም አቀፋዊ መሆኑን ገልፀው በምናከናውናቸው የሰላም ግንባታ ስራዎች እቅድ ላይ በማካተት ሴቶች በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ልናረጋገጥ ይገባል ብለዋል ። አያይዘውም ይህ የሰላም ግንባታ ስርዓተ-ፆታ ማካተቻ ስትራቴጂ የማካተት ተግባራችን የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የሚያግዝ ነው በማለት ገልፀዋል።
የዩኤን ውሜን ኢትዮጵያ የሴቶች ሰላምና ደህንነት ፕሮግራም ኦፊሰር አቶ ነጋ ገርባባ በበኩላቸው ዩኤን ውሜን ኢትዮጵያ የሴቶችን ሰላምና ደህንነት ከሚያስጠብቁ ተቋማት ጋር እየሰራ ሲሆን ከነዚህም ተቋማት መካከል አንዱ የሰላም ሚኒስቴር ነው ብለዋል። ግጭቶች ሲከሰቱ የመጀሪመያ ገፈት ቀማሾች ሴቶች ናቸው ግጭቶችንም በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ሴቶች ጉልህ ሚና አላቸው ይህን ሚናቸው በአግባቡ እንዲወጡ የሰላም ግንባታ ስርዓተ-ፆታ ማካተቻ ስትራቴጂ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል በማለት ገልፀዋል።
የስርዓተ -ፆታ ማካተቻ ስትራቴጂ ለውይይቱ ተሳታፊዎች ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቶበታል።
የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ባለሙያዎች ፣የክልልና ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ የስራ ሃላፊዎች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።