የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ጥቅሞች --- ከባለፈው የቀጠለ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር በአገራዊ የጋራ ማንነቶች፣ ጥቅሞችና እና እሴቶች ላይ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ልማት መሰረት መሆኑን በመረዳት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

እንደ ሀገር በሁሉም ነገር ላይ መግባባት ላይ መድረስ ባይጠበቅብንም በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረስ እና ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለይቶ ማወቅ ግን ለዘላቂ ሰላማች እና አንድነታችን መሰረት ነው፡፡

ብሔራዊ ጥቅሞቻችን ከታሪካችን፣ ከሕገ-መንግስቱ፣ የውጭ ግንኙነት/ጉዳይ ሰነዶች፣ ከተለያዩ ሀገራዊ ፖሊሲዎች ሰነዶች፣ ሀገራችን ላይ አሁን እየታየ ካለው ነባራዊ ሁኔታ እና የሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ እንፃር በመነሳት ‘’የኢትዮጵያ ሀገራዊ ጥቅም’’ የሚከተሉት ጉዳዮችን ይዟል፦ ከባለፈው የቀጠለ …

7. የትምህርት ጥራት

የጠንካራ ሀገር መሰረት ጠንካራና ታታሪ ዜጎች ናቸው፡፡ ጥራት ያለው ትምህርት ዜጎች እንዲያገኙ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ሙያዊ፣ ሞራላዊና አካላዊ ብቃትን ለትውልድ የሚያጎናፅፍ ጥራት ያለው ትምህርት ለኛ የሀገር ሕልውና ጉዳይ ነው ፡፡

8.ማህበራዊ ሃብቶች

ባህላዊ እሴቶቻችን የማንነት መሰረት ናቸው፡፡ ባህሉን ያጣ ሕዝብ ለማንነት ቀውስ ይጋለጣል፡፡ በማንነት ቀውስ የተጠቃ ህዝብ ደግሞ ተባብሮ የጋራ አጀንዳ ለማሳካት አይችልም፡፡ መሰረታዊ ባህላዊ እሴቶቻችንን መንከባከብና መጠቀም የህልውና ጉዳይ ነው፡፡

9. የሕዳሴው ግድብ

ይህ የህዳሴው ግድብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ አንደኛው የይቻላል መንፈስን ለኢትዮጵያውያን ማጎናፀፍ ነው፡፡ ሁለተኛው የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጥቅሙ ነው፡፡ ሦስተኛው ቀጠናዊ ትስስር መፍጠሩ ነው፡፡

10. ሀገር በቀል እውቀቶች/ፈጠራ

አሁን ላይ ውድድር በእውቀት ሆኗል፡፡ እውቀትን ቀድሞ መፍጠር የቻለ በአሸናፊነት ይገሰግሳል፡፡ ሀገር በቀል እውቀት የሌለው ሀገር ግን የሰው ሸቀጥና ሀሳብ ማራገፊያ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሀገር በቀል እውቀቶቻችንን ማበልፀግና መጠቀም አንደኛው ሀገራዊ ጥቅም ነው፡፡

11. ስነ-ህዝብ እና ሰብዓዊ ልማት

ከፍተኛ የወጣት ህዝብ ቁጥር ያላት ሃገራችን የስነ-ህዝብ ሂደቶችን መቆጣጠር ካልቻለች ለከፍተኛ የደህንነትና አለመረጋገት ሁኔታ ሊያጋልጣት ይችላል።

12. ቀጠናዊ /አህጉራዊ ትብብሮች ናቸው፡፡