የሰላም ሚኒስቴር ከሲ አር ኤስ (catholic relief services) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ዛሬ መስከረም 23/2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከሲ አር ኤስ (catholic relief services) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ የሰላም ሚኒስቴር ግጭቶችን ከመፍታትና ከመከላከል ፣ የሰላም ግንባታ ስራዎችን በጋራ ለመስራት እና ግጭቶች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች ተፈናቃዮችን መልሶ በማቋቋም ሂደት ውስጥ ለሚያከናውናቸው ተግባራት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ስምምነት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ እና የሲ አር ኤስ በኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ዘመዴ ዘውዴ ስምምነቱን ተፈራርመዋል ፡፡-