ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ቡድን በሞሮኮ የልምድ ልውውጥ አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ቡድኑ የሰላምና ፀጥታ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ ኃላፊዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች የተካተቱበት ነው። ጉብኝቱን ያስተባበረው የሰላም ሚኒስቴር ነው።May be an image of 9 people and toy

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክር የገለጹት የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ሞሮኮ የተለያዩ ሃይማኖቶችና ሕዝቦችን ተከባብረው እንዲኖሩ በማድረግ በአፍሪካ ጠንካራ ኢኮኖሚ የገነባችበት መንገድ ለሀገራችን ጥሩ ልምድ ይሆናል ብለዋል::May be an image of 10 people and dais

የልዑካን ቡድኑ በሞሮኮ ዋና ከተማዋ ራባትን እና ዋና የንግድ ከተማ የሆነችውን ካዛብላንካን ጨምሮ በአራት ትላልቅ ከተሞች ላይ የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማትን ይጎበኛል። ከተቋማቱ ኃላፊዎችም ጋር ይነጋገራል ተብሏል።