ምክር ቤቶቻችን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገር ግንባታ ስኬቶቻችን

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሚያዝያ 23/2016 .ምክር ቤቶቻችን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገር ግንባታ ስኬቶቻችንበሚል መሪ ሐሳብ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች እና የክልልና ከተማ አስተዳደር አፈ-ጉባዔዎች በሀገር መሠረታዊያን ዙሪያ የተዘጋጀ የስልጠናና ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡

መርሐ ግብሩ አዲሱ ገዢ ትርክት በትውልዱ እንዲቀረጽ ምክር ቤቶች እና አፈ-ጉባዔዎች በየደረጃው ከሚኖራቸው የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ጋር በማስተሳሰር እንዲሠሩ ንቅናቄ የመፍጠር ዓላማ ያለው ነው፡፡ 

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ዘላቂ ሰላምና ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ብሔራዊ መግባባት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበው በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣት ሀገራዊ ማንነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና የጋራ እሴቶች በሚሉ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ብሔራዊ መግባባት በውይይት የሚመጣ መሆኑን እና ይህንንም ለማሳካት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩነጠላ ትርክቶችን ማዕከል አድርገው የጋራ ማንነቶችን የሚሸረሽሩ ትርክቶች እየበዙ በመሆኑ በገዢ ትርክት ላይ የሚያተኩሩ እና በሀገራዊ ማንነታችን ላይ መግባባት የሚፈጥሩ ሥራዎችን መሥራት አስፈላጊ መሆኑን፣ ኢትዮጵያዊያን የተጋመድንባቸው የጋራ እሴቶቻችን ብዙ ቢሆኑም እነዚህን የሚሸረሽሩ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ በመምጣታቸው፣ ያሉንን መልካም እሴቶች እንድናሸጋግራቸውና ትውልዶች እንዲረከቡ ማድረግ ብሎም ብሔራዊ ጥቅሞቻችን ማስጠበቅ ቁልፍ የብሔራዊ መግባባት አጀንዳዎቻችን ናቸውብለዋል፡፡ አክለውምብሔራዊ መግባባትን እንዴት እንፍጠር” በሚለው ነጥብ ከባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት በሚሠሩ ጉዳዮች  ላይ ማብራሪያ ሰጥተው ምክር ቤቶቹ የሰላም ግንባታ ሥራውን እንዲደግፉ እና ንቅናቄው እስከታችኛው እርከን ወርዶ ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ክቡር ከይረዲን ተዘራ (/) የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታምክር ቤቶቻችን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገር ግንባታ ስኬቶቻችንበሚል ርዕስ እንዲሁምየሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነትበሚል ርዕስ በሚኒስቴሩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚና የሚኒስትር /ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ አቶ አዱኛ በቀለ የመወያያ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመድረኩ የጋራ እሴቶቻችን ለችግሮቻችን መፍቻና ለሀገር ግንባታ ያላቸው ሚና ትልቅ ስለሆነ ዕውቅና ተሰጥቷቸው ከነባሩ ባህሎቻችንና የሌሎችም ተሞክሮ ተወስዶ በመንግሥት፣ በማኅበረሰብ እና በግለሰብ ደረጃ ሊተገበሩ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

ሀገራችን አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ዘላቂ ሰላምን የሚያመጡ፣ አንድነታችንን የሚያጠናክሩ፣ ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥሩና ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን የሚያስጠብቁ ተቋማትን የማጠናከር እና የህግ ማዕቀፎችን የማዘጋጀት ተግባር ትኩረት እንዲደረግባት የመድረኩ ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡