የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 129ኛው የአድዋ የድል በዓልን አከበሩ
የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 129ኛው የአድዋ የድል በዓልን አከበሩ
የካቲት 25/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 129ኛው የአድዋ የድል በዓልን “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አክብረዋል።
በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና የግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ የአድዋ ድል የአለምን ታሪክ ከቀየሩ ሁነቶች አንዱ ነው ያሉ ሲሆን ድሉ የሁሉም ጥቁር ህዝቦች ድል ነው ብለዋል።
ከአድዋ ድል የዓላማ ፅናትን፣ አንድነትን፣ ሃገርን ማስቀደምን፣ የሀገር ፍቅርን ፣የመንፈስ ጥንካሬን፣ ጽናትን እና የአልሸነፍ ባይነት ወኔን በዚህ ዘመን ያለን ኢትዮጵያዊያን ልንማር ይገባል ብለዋል፡፡
አድዋ ለሀገር ግንባታ ያለው ፋይዳ ትልቅ ነው ያሉት ክቡር አቶ ቸሩጌታ አድዋ የጋራ ማንነት/ ምናብ/ ይዘው የተነሱ ኢትዮጵያዊያን ውጤት ነው ያሉ ሲሆን ሀገርን የሚያቋማት ይሄው የጋራ ማንነት /ምናብ/ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ክቡር አቶ ቸሩ ጌታ አክለውም እኛ በጣም እድለኛ ህዝቦች ነን፤ እንደ አድዋ ያሉ ግዙፍ የጋራ ማንነነቶች አሉን ያሉ ሲሆን ይህን ማንነት ለህብረ ብሔራዊ አንድነትና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ልናውለው ይገባል ብለዋል፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ የአድዋን የድል በዓል የተመለከቱ ጥያቄና መልሶች፣ መጣጥፎች፣መነባንብ፣ግጥሞች፣ እና ሌሎች የኪነ ጥበብ ሥራዎች ቀርበዋል፡፡