የሞሮኮ ልዑክ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲና የካቴድራሉ ሙዚየም ጉብኝት አደረገ
የሞሮኮ ልዑክ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲና የካቴድራሉ ሙዚየም ጉብኝት አደረገ
የካቲት 17/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማትን፣ ቅርሶችን እና ታሪካዊ ቦታዎችን ሲጉበኝ የቆየው የሞሮኮ ልዑክ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲና የካቴድራሉን ሙዚየም ጎብኝቷል፡፡
ልዑካኑን ያስጎበኙት ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሊቀ ጳጳስ ቤተክርስቲያኗ በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ትውልዱን በማነጽ፤ በትምህርትና በሌሎች የልማት ዘርፎች በስፋት በመሳተፍ እያከናወነች ያለው ተግባር ለመላው አፍሪካ መልካም ተሞክሮ የሚሆን ስለሆነ ልምድ ወስዶ መተግበር ለዕድገትና ሥልጣኔ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ መሪ በሞሮኮ የመሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ሰክሬተሪ የሆኑት ዶ/ር መሐመድ ረፊቅ በበኩላቸው “አፍሪካዊያን የነበረንን ቀደምት ስልጣኔ እና ልምዶቻችንን ቀምረን፤ ትብብራችንን አጠናክረን በጋራ ሠርተን ለትውልድ የሚሻገር ታሪክ መሥራት አለብን”፤ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡