''ጠንካራ ተቋማት ሲኖሩ ጠንካራ ሀገር ይኖራል'' ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሚያዚያ  19 ቀን 2016 . የሰላም ማኒስቴር በተቋሙ ተግባር እና ሃላፊነት ፣እያከናወናቸው ባሉ ተግባራት እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ለሰራተኞቹ  ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የውይይት መድረክ ተጠናቋል።

በዛሬው የስልጠና እና የውይይት መድረክ ላይ  የየ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ወይይት የተደረገ ሲሆን በመደመር መፅሐፍ ላይም  ገለፃ ተደርጓል።

የዛሬውን መድረክ የመሩት የሰላም ሚኒስቴር የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መብራቱ ካሣ  በስልጠናው ያገኘናቸውን ዕውቀቶችና ክህሎቶች ወደ ተግባር በመቀየር ለተቋሙ ውጤታማነት መስራት ይገባናል ብለዋል፡፡ አክለውም  የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ጊዜው የሚጠይቀውን የቴክኖሎጅ እና አለማቀፋዊ ሁኔታውን በመረዳት ራስን ዝግጁ ማድረግ  ይገባልም ብለዋል።

መድረኩን ያጠቃለሉት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ  ክቡር / ከይረዲን ተዘራ ተቋሙ እያከናወናቸው ባሉ ተግባራት ላይ ሁሉም ሰራተኛ ሚና አለው ያሉ ሲሆን ተቋም የሚያድገው በአንድነት መንፈስ መስራት ስንችል ነው ብለዋል።

ሚኒስትር ዴዔታው አክለውም ሰላም ሚኒስቴር የተቋም ግንባታ ላይ የሚሰራ ተቋም ነው ያሉ ሲሆን ጠንካራ ተቋማት ሲኖር ጠንካራ ሀገር ይኖራል ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ተቋማችን ትልልቅ ሀገራዊ ንቅናቄዎችን እና የዘመቻ ሥራዎችን እያደረገ ይገኛል ያሉት ክቡር / ከይረዲን ተዘራ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ለውጤታማነቱ በትጋት ልትሰሩ ይገባል ብለዋል።