የደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባ ክልሎች ለጋራ ተጠቃሚነት ተወያዩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሚያዝያ 16/2016 . የደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባ ክልሎች በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚ በሚያደርጓቸው የጋራ ጉዳዮች ምክክር አድርገዋል፡፡

መድረኩ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በቅንጅት የተዘጋጀ ሲሆን የክልሎችን የርስ በርስ የመንግሥታትቀ ግንኙነት ሥርዓትን በማጠናከር በክልሎቹ የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት  የማረጋገጥ ዓላማ ያለው ነው፡፡ 

የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባዔ የተከበሩ / ሰዓዳ አብዱራህማን በምክክር መድረኩ ተገኝተው ባሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግርችግር ፈቺና የክልሎችን የጋራ ጥቅም የሚያረጋግጥ የመንግሥታት ግንኙነት  ሰላምን ለማስፈን፣  የጋራ ልማትን ለማፋጠን ወሳኝ የሆኑ የግንኙነት መድረኮችን ማቋቋም የተጎራባች ክልሎች የግንኙነት መድረክ  መመስረት ድርሻው ትልቅ ነውሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ 

የፌደሬሽን ምክር ቤት የመንግሥታት ግንኙነት የዲሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገ-መንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ የሆኑት የተከበሩ / ባንቺይርጋ መለሰዘላቂ ሰላምን ለማስፈን፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ፣ ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ለማስቀጠልና አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን ለመገንባት ይቻል ዘንድ ከተናጠል ጥረቶች ይልቅ የየእርከኑን አካላት አቅሞች በተገቢው መንገድ አቀናጅቶና አዋህዶ ዘርፈ-ብዙ የልማትም ሆነ የመልካም አስተዳደር ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችሉ መደበኛ የመንግስታት ግንኙነቶች መኖር በጣም አስፈላጊ ነውብለዋል፡፡

ውይይቱን የመሩት የሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ የተጠናከረ የመንግሥታት ግንኙነት ሥርዓት በመዘርጋት ክልሎች ሕዝብን የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን በትብብር በመሥራት፤ የማኅበረሰቡን ችግር የሚፈቱ መሠረተ ልማቶችን  በፍትሐዊነት ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ  ለሰላም፣ ለእድገትና ልማት ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑን አስገንዝበው ክልሎች ያሏቸውን ሃብት እና አቅም ተጠቅመው አጠቃላይ ሀገራዊ ልማትንና ሰላምን የሚያሳልጥ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

ውጤታማ የተጎራባች ክልሎች የግንኙነት ሥርዓት መፍጠር ህብረብሔራዊ አንድነትን እና ማኅበረሰባዊ ግንኙነትን የማጠናከር፤ ውጤታማ የመንግስታት ግንኙነት ስርዓት በመገንባት  ክፍተቶችን በመሙላት ፌዴራላዊ ስርዓቱንም ሆነ የሀገሪቱን ዲሞክራሲያዊ አንድነት እውን እንዲሆን ክልሎች ግንኙነታቸው ተጠናክሮ፣ ችግሮችን በጋራ እየፈቱ የጋራ ሰላም እንዲጠበቅ ተቀናጅቶ መሥራት ያስፈልጋል ሲሉም ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡