''ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም በሚል መሪ ሃሳብ '' ሀገር አቀፍ የሩጫ ውድድር ሊካሄድ ነው
''ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም በሚል መሪ ሃሳብ '' ሀገር አቀፍ የሩጫ ውድድር ሊካሄድ ነው
ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣የሰላም ሚኒስቴር ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመቀናጀት ''ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም በሚል መሪ ሃሳብ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚካሄድ ይሆናል።
የሩጫውን መርሃ ግብር እና አጠቃላይ ሂደቱን አስመልክቶ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና የብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ከታላቁ ሩጫ አዘጋጆች እና ከሰላም ሚኒስቴር ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል።
ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ የሩጫው ዓላማ በሀገራችን የተገኘ ያለውን አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማሸጋገር ዜጎች በአገር መንግስት ግንባታ ሂደት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ ሩጫ የእናት ሀገር ጥሪ ጭምር ነው ያሉት ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ሩጫው ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሰላም ጉዳይ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ ለማስተላለፍ ነው ብለዋል።
ሩጫው 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን በሰኔ ወር የሚካሄድ ይሆናል። በአዲስ አበባ ብቻ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች በሩጫው የሚሳተፉ ሲሆን በውድድሩ ለሚያሸንፉ የገንዘብ እና የሜዳልያ ሽልማት የሚበረከት ይሆናል።