ሀገራዊ ምክክሩን አስመልክቶ ከፋይናንስ ተቋማት እና ከልማት ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ሀገራዊ ምክክሩን አስመልክቶ ከፋይናንስ ተቋማት እና ከልማት ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሄደ

ህዳር 8/2015 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር) ''የፋይናንስ ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች በሃገራዊ ምክክሩ ላይ ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ከፋይናንስ ተቋማትና ከልማት ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል ።

ወይይትቱን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደኣ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ዋና መሠረት የፖለቲካ ጤንነት ነው ያሉ ሲሆን ይህም የሚሳከው ዜጎች በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው መግባባት ላይ ሲደርሱ ነው ብለዋል ።

በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወይታቶ መግባባት ላይ መድረስ የውዴታ ግዴታ ነው ያሉት አቶ ታዬ ሀገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን የፋይናስ ተቋማትና የልማት ድርጅቶች ንቁ ተሣትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ።

ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተቋቋመ ቢሆንም ኮሚሽኑ ውጤታማ እንዲሆን የሁሉም ተቋማት ድጋፍና ተሣትፎ እንደሚያስፈልግ አቶ ታዬ ተናግረዋል ።

''የብሔራዊ ምክክር መሰረታዊያን ፣ንድፍ-ሃሳቦች ፣ልምዶች እና በሀገራችን ያለበት ደረጃ '' የሚል ፅሁፍ በሰላም ሚኒስቴር የብሔራዊ መግባባት ዴስክ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ገዛኸኝ ጥላሁን እና ''ለሃገራዊ የምክክር ሂደቱ ስኬት የፋይናንስ ተቋማትና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚና '' የሚል ፅሁፍ የኢኒሽዬቲቨ አፍሪካ ዋና ዳይሪክተር በሆኑት በአቶ ክቡር ገና ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል ።

የምክክር መድረኩን የሰላም ሚኒስቴር፣የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና ኢኒሸዬቲቨ አፍሪካ በጋራ አዘጋጅተውታል ።