የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ መሰረቱን አሜሪካ ካደረገው ስተርሊን ፋውንዴሽን ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ መሰረቱን አሜሪካ ካደረገው ስተርሊን ፋውንዴሽን ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በውይይቱ ለተገኙ የስተርሊን ፋውንዴሽን ሃላፊዎች የሰላም ሚኒስቴር እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት በተለይም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት እና መሰረታዊ የሀገር መንግስት ግንባታ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ለማድረግ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።

 

ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ አክለውም የሰላም ሚኒስቴር የዘላቂ ሰላም ስራዎችን እና የብሔራዊ መግባባት ተግባራትን ለማጎልበት በሰላም ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን የዛሬው ውይይትም የዚህ አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡

 

ከስተርሊን ፋውንዴሽን የመጡ ኃላፊዎች በበኩላቸው ከሰላም ሚኒስቴር አመራሮች ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ አመስግነው በቀጣይ ከተቋሙ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል