6ኛውን ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ ምክክር መድረክ በጋምቤላ ከተማ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የካቲት 15 እና 16 ቀን 2016 .ም የሰላም ሚኒስቴር ከጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመተባበር 6ኛውን ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ ምክክር መድረክ በጋምቤላ ከተማ አካሂዷል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም የአንድ ሀገር እድገት መሠረቱ ሰላም ነው ያሉ ሲሆን መንግስት  ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ሀገራዊ አጀንዳዎች መካከል ዘላቂ ሰላም መገንባት እና ብሔራዊ መግባባት ማጎልበት ቀዳሚ ቦታ ይይዛሉ ብለዋል።

የሰላም ግንባታ ስራ የማያቋርጥ ድርድርና ውይይት ይጠይቃል ያሉት ክቡር አቶ ብናልፍ ለረጅም ጊዜ እየተጎተቱ በመጡ መጥፎ የፖለቲካ ባህላችን እና የተዛቡ ትርክቶ ምክንያት ሰላማችን እየደፈረሰ ይገኛል ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላም ለመገንባት እና ብሔራዊ መግባባት ለማጎልበት ትልልቅ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የገለፁት ክቡር  ሚኒስትሩ ከክልልና ከፌዴራል የሰላምና የፀጥታ ተቋማት ጋር በትብቡር መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የመድረኩ ዓላማ በአለፉት ስድስት ወራት በሀገራችን ያለውን የሰላምና ፀጥታ በመገምገም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በማረም፣ የቀጣይ 6 ወራት ዕቅድን የጋራ በማድረግ አውንታዊ የሠላም ግንባታ ሂደት ውጤታማ ማድረግ  ያለመ  መሆኑን ክቡር ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ  መልእክት ያስተላለፉት ጋምቤላ የህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ኡመድ ኡጅሉ  በበኩላቸው ክልሉ ባለው ውስን የፀጥታ ሃይል ምክንያት እና በክልሉ ድንበር  አካባቢ በሚከሰቱ ወንጀሎች  አልፎ አልፎ የሰላም መደፍረሶች እያጋጠሙት ይገኛሉ ያሉ ሲሆን ይህን ለመከላከል እንስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

በየጊዜው በሚያጋጥሙን የሰላም መደፍረስ ምክንያት ልማት ላይ እንዳናተኩር አድረርጎናል ያሉት አቶ ኡመድ አስተማማኝ ያለው ሰላም ለመገንባት የሁሉም ዜጋ ቅንጅታዊ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ ''የሰላም ሚኒስቴር 2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት''  የሰላም ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በሆኑት  በአቶ አዱኛ በቀለ፤  ''5ተኛው የፌዴራልና የክልሎች የፀጥታ አካላት የጋራ መድረክ የተቀመጠው አቅጣጫ አፈፃፀም ሱፐርቪዥን ሪፖርት'' የሰላም ሚኒስትር አማካሪ በሆኑት በአምባሳደር እሸቱ ደሴ እና ''የኢትዮጵያ የፌዴራል ፖሊስ 2016 በጀት ዓመት 6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት'' የፌዴራል ፖሊስ  /ኮሚሽነር  በሆኑት ኢሳቅ አሊ መሀመድ በኩል ቀርበዋል።

በመድረኩ ላይ ከፌዴራል እና ከክልል ተቋማት የተገኙ አመራሮች  በሰላምና በፀጥታው ዘርፍ ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ተግባራትንና ተሞክሮዎች፣ያጋጠማቸውን ችግሮች በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጓል።

ከመድረክ ለተነሱ ሃሳቦች ማጠቃለያ የሰጡት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም  በአለፉት ስድስት ወራት ትልልቅ ስራዎች የተሰሩበት ወቅት ነበር ያሉ ሲሆን  የሰላም ግንባታ ስራ በሆነ ፀጥታ ተቋማት ጥረት ብቻ የሚሰፍን አድርገው የሚያስቡ ሰዎች አሉ ዕውነታው ግን ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው  በእያንዳንዱ ግለሰብ በሚመጣ የአወንታዊ ሰላም የአስተሳሰብ ለውጥ ነው ብለዋል።

 በእየደረጃው ያለ  አመራር በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት ተግባሩን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል  ያሉት ክቡር አቶ ብናልፍ  የሊህቃን የሐይማኖት ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማትና የሚዲያ ተቋማት ተሳትፎ  ለሀገራዊ ሰላም ግንባታ የማይተካ ሚና  ያላቸው በመሆኑ በቀጣይ ከነዚህ ተቋማት ጋር ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

 

በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተን የጋራ አቋም መያዝ ይኖርብናል ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ስርዓት ይቀያየራል ሀገርና ህዝብ ግን ይቀጥላል ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር / ከይረዲን ተዘራ በበኩላቸው ይህ መድረክ ሀገራዊ የሰላም ሁኔታ ምን እንደሚመስል የዳሰስንበት ነው ያሉ ሲሆን እንደ ሀገር ያለውን የሰላም ችግር ፈትተን ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር ለመገንባት የበለጠ ቁርጠኛ መሆን ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።

አመራሩ ለሰላሙ ቁርጠኛ ሆኖ መስራት ከቻለ ብዙ ነገሮች መሻሻል ይችላሉ ያሉት ሚኒስትሩ ዴዔታው  ህዝብን ታች ድረስ ወርዶ ማወያየትና ችግሩን ማዳመጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

መድረኩ ለቀጣይ ስራችን ላይ ግብዓት ያገኘንበት ነው  ያሉት ደግሞ የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ ናቸው።

ክቡር አቶ ቸሩጌታ አክለውም የሰላም ግንባታ ስራ ተከታታይ ጥረት ይጠይቃል ያሉ ሲሆን በአመራሮች መካከል መተማመንና ቅንጅታዊ አሰራር ሊጎለብት ይገባል ብለዋል።

ለጠንካራ ሰላም ግንባታ መተማመንና የተረጋጋ ስነ ልቦና ያስፈልጋል ያሉት ክቡር አቶ ቸሩጌታ  የፀጥታ ችግሮች ተሻጋሪ በመሆናቸው እና የአንዱ ሰላም መደፍረስ ሌላውም ላይ ያለው ተፅኖ ከፍተኛ  በመሆኑ  ለመፍትሄ ሁሉም አካል በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ አክለዋል።

በመድረኩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የውጭ ግንኙነትና የሰላም ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች፣የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ ተቋማት  ከፍተኛ አመራሮች፣የክልል ከፍተኛ አመራሮች ፣እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።