ከአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት (USAID) እና ከዩኤስ አይዲ አጋር ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ እና የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ ከአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት (USAID) እና  ከዩኤስ አይዲ አጋር ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በውይይቱ ለተገኙ ዩኤስ አይዲ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ ስላለው የሰላም ሁኔታ በዝርዝር ያብራሩ ሲሆን የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና መሰረታዊ የሀገር መንግስት ግንባታ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

የሰላም ስራ በተናጠል ብቻ የሚሰራ ባለመሆኑ የሰላም ሚኒስቴር  በሰላም ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅርበት መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ዶ/ር ከይረዲን  የሰላም ግንባታ ስራዎቸ እና የሀገረ መንግስት ግንባታ ተልዕኳችን ውጤማ የሚያደረጉ ሀገራዊ ንቅናቄዎች እየተደረጉ ይገኛሉም ብለዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር በሀገራችን ዘላቂ የሆነ ሰላም ለመገንባት  የሚሰራ ተቋም ነው ያሉት ደግሞ የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ ናቸው፡፡ክቡር አቶ ቸሩጌታ ስለ ሰላም የሚሠሩ ሥራዎች ውጤታማ ሆነው በቀጣይ በሀገራችን አዎንታዊ ሰላም እንዲሰፍን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራታችን ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ከዩኤስ አይዲ የመጡ ኃላፊዎች በበኩላቸው ከሰላም ሚኒስቴር አመራሮች ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ አመስግነው በቀጣይ ከተቋሙ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል