"የሰላም ግንባታ የዕለት ተዕለት ተግባርና ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ይጠይቃል'' ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የካቲት 06/2016 ዓም (ሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ከድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት/VSO/ ጋር በመተባበር  የሰላም የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ስራ  የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሂዷል።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘረፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር / ከይረዲን ተዘራ የሰላም ሚኒስቴር ዋና ተልዕኮው አዎንታዊ አስተሳሰቦችን በትውልዱ አዕምሮ ውስጥ መቅረፅ ነው ያሉ ሲሆን ይህን ለማሳካትም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን 2013 . ጀምሮ በጎነት ለአብሮነት በሚል መሪ ሃሳብ የሰላም ብሄራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት በመንደፍ  ወጣቱ ትውልድ  በዘላቂ ሰላም ግንባታ እና በሀገር ግንባታ ሥራ ላይ  የራሳቸውን አስተዋጾ እንዲያበረክቱ  እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ወጣቱ ትውልድ ሁለንተናዊ ሠላም ከማስፈን አንጻር የማይተካ ሚና አለው ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው የሰላም ብሄራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ዓላማ  ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን እና መርሆቻችን ለወጣቱ ትውልድ በማስተላለፍ የወጣቶችን የሀገር እና የሕዝብ ፍቅርን፣ ምክንያታዊነት፣ የሕይወት መምራት ክሕሎትን፣ የሥራ ባሕልን፣ ሥነ ምግባር በማጎልበት የተከበረች እና ታላቅ ሀገር መገንባት መሆኑን ተናግረዋል።

 የሰላም ግንባታ የዕለት ተዕለት ተግባርና ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ይጠይቃል ያሉት ክቡር / ከይረዲን  የሰላምና ሀገር ግንባታ ስራ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ  የሚጠይቅ በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የዛሬው ውይይት ዓላማ ለሰላም ብሄራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም   ድጋፍ ላደረጉ አካላት ዕውቅና ለመስጠት እና በቀጣይ አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳይ ላይ ለመመካከር መሆኑን ክቡር / ከይረዲን  ገልፀዋል።

የድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት/VSO/  ተወካይ አቶ ተመስገን አለሙ  በበኩላቸው ድርጅታቸው በወጣቶች ላይ የሚሰራ ድርጅት መሆኑን ገልፀው ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በርካታ ስራዎችን ሰርቷል በቀጣይም ይህን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ ''የሰላም ብሄራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት እና ያጋጠሙ ችግሮች'' የሚል ሰነድ  የሰላም ሚኒስቴር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ በሆኑት በአቶ ገመቺስ ኢቲቻ  እና  ''የድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት/VSO/ የተቋቋመበት ዓላማ እና ያከናወናቸው ተግባራት'' የሚል ሰነድ ደግሞ  የድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት/VSO/ ባለሙያ በሆኑት በአቶ ተመስገን ቢረዳ ቀርቦ ወይይት ተደርጎባቸዋል።

የህዝብ ተወካዮች  /ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የፌዴራል መንግሰት ተቋማት አመራሮች የኢትጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች፣ ዓለም አቀፍ ተራዶ ድርጅቶች፣ ሀገር በቀል ተራዶ ድርጅቶች እና የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።