የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር እና የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ውይይት አካሄዱ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የካቲት 5/2016 . (ሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት  በጋራ ጉዳዮች( ማንዴቶችላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል፡፡

 ውይይቱን ያስጀመሩት የተከበሩ አቶ ፍቅሬ አማን በኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ አስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ ሲሆኑ የውይይት መድረኩ ዓላማ በመንግስታት ግንኙነቶች፣ በሰላም ግንባታ ሂደቶች፣ በግጭት አፈታት እና በብሔራዊ መግባባት ዙሪያ በሚታዩት ችግሮች ላይ ውይይት ለማድረግ እና የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

 የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር መሰረት ግጭት አፈታት እና የሰላም ግንባታ ስራን በተመለከተ ስትራቴጂክ ዕቅድ በማዘጋጀት እና የአሰራር ማሻሻያ በማድረግ ዘመናዊ እና ባሕላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም በርካታ ስራዎችን እየሰራ ቢሆንም ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በጋራ መስራቱ ይበልጥ ውጤታማ እንደምያደርገው በማመን ይህንን መድረክ ለማዘጋጀት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት በተለይም በሰላም ግንባታ እና በብሔራዊ መግባባት ጉዳዮች ዙሪያ በተናጠል ከመስራት ይልቅ በጋራ እና በተጠናከረ ቅንጅት መስራት ተልዕኮውን ውጤታማ እንደሚያደርገው በማመን ቅንጅታዊ ስራ እንዲጠናከር አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

 ከአሁን በፊት በመንግስታት ግንኙነት ዙሪያ በጋራ መስራት ቢቻልም የተፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት አለመቻሉን አውስተው በጋራ መስራቱ የሀብት ብክነትን፣ ጊዜን፣ ጉልበትን እና አቅምን እንደሚቆጥብ ገልጸው ከዚህም በላይ ግልጸኝነትን እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ  ክቡር / ከይረዲን ተዘራ በበኩላቸው ለቅንጅታዊ ስራው ተነሳሽትን የወሰደውን የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን አድንቀው ለስራው ስኬታማነት የአመራር ቁርጠኝነት፣ ጠንካራ ቅንጅት፣ በሙሉ አቅም መንቀሳቀስ ውጤታማ እንደሚያደርግ በመናገር በጋራ እቅድ እንዲመራ አሳስበዋል፡፡

 በመጨረሻም ሁለቱ ተቋማት የማስፈጸሚያ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የመግባቢያ ሰነድ እንዲዘጋጅ እና የተቋማቱ ከፍተኛ አመራር አካላት በተገኙበት እንዲፈራረሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር / ከይረዲን ተዘራ፣ የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ፣የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰን፣ እና የሠላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና የዳሬክቶሬቱ ከከፍተኛ ባለሙያዎች እና የመንግስታት ግኝኑነት፣ የዲሞክራሲ አንድነት እና የሕገ መንግስት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።መረጃው የተገኘው  ከኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌስቡክ ገፅ ነው።