ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች እና የባለድርሻ አካላት ሚና

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 9 ቀን 2016 . (የሰላም ሚኒስቴር) “ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች እና የባለድርሻ አካላት ሚና በኢትዮጵያበሚል ርዕስ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት ጋር በትብብር የተዘጋጀ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱ ለሰላም ግንባታው የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት የማጠናከር ዓላማ ያለው ነው፡፡

 

የውይይት መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሚድያ ባለሙያዎች፣ ምሁራን እና የውጭ አጋር አካላት የታደሙበት ነው፡፡ 

መድረኩን በንግግር የከፈቱት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነየሰላም ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን ለሰላም እጦት ምክንያት የሚሆኑ እንቅፋቶችን በውይይት በመፍታት፤ ሰላምን ለማምጣት ሁላችንም ኃላፊነታችንን መወጣት፣ መተጋገዝ እና በትብብር መሥራት አለብንሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር / ሀና ወልደገብርኤል /ቤቱ ወሳኝና አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተለይም በሰላም ዙሪያ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ ተሃድሶ ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ /ቤት ጋር መርህን መሠረት ያደረገ ግንኙነት በመፍጠር የበኩሉን አስተዋጽዖ በማበርከት ለዘለቄታዊ ሰላም ዘርፈ-ብዙ ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

/ ሀና በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች የተከሰቱ እና ቀጥለው የሚገኙ ግጭቶች ሀገሪቱን በጽኑ እየተፈታተኗት ባለበት በአሁኑ ወቅት ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን እና የባለድርሻ አካላትን ሚና ለማጎልበት የምንወያይበት አጀንዳ ሁላችንም ሚናችንን በጥልቀት በመመርመር በኢትዮጵያ አውድ የተቃኘ ዘላቂ የሰላም መፍትሔዎችን ለመለየት የሚረዳ መድረክ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ 

በውይይት መድረኩ ከሀገር በቀል የግጭት መፍቻ እሴቶች ጋር በተገናኘ በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ምሁራን አማካይነት የተጠኑ ጥናቶች ቀርበዋል፡፡ በቀረቡ የጥናት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡  ግጭቶች ከመከሰታቸው እና ችግር ከማስከተላቸው በፊት በመከላከል ላይ ትኩረት እንዲደረግ ተሳታፊዎች አሳስበዋል፡፡