ህብረተሰብ-ዓቀፍ የክልል፣ የከተማ አስተዳደር፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮች ውይይት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

የሰላም ሚኒስቴር ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ከተወጣጡ የክልል፣ የከተማ አስተዳደር፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ጋር በሀገራዊ የምክክር ሂደቶች ላይ ውይይት አድርጓል።

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስቴር የአቅም ግንባታና ተቋም ማዘመን ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አለማየሁ እጅጉ ያለንበት የለውጥ ሂደት በአዳዲስ እሳቤዎች የታጀበና በሚታዩና በሚጨበጡ ድሎች ያሸበረቀ ቢሆንም በርካታ ፈተናዎችንም ማለፍ ይጠበቅብናል ብለዋል። መድረኩ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በየጊዜዉ የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች በብልሀትና በመናበብ ማለፍ እንችል ዘንድ የተዘጋጀ መሆኑንም ገልፀዋል።

አክለዉም በየደረጃዉ ያሉ አመራሮች የተሰጣችሁን ህዞባዊ ኃላፊነት ለመወጣት ወቅቱን ባገናዘበ ሁኔታ በመላው የአገራችን ክፍል ምቹ፣ ስልጡን፣ እውነተኛና ዴሞክራሲያዊ አሰራር እንዲዳብር መስራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

ሰላም የስራችን ሁሉ መነሻና መድረሻ ነው ያሉት ክቡር አቶ አለማየሁ ሰላም የሁሉንም ዜጋ ጥበቃ፣ ትኩረትና የነቃ ተሳትፎ ይፈልጋል ብለዋል።

ይህ መድረክ የሰላም ሚኒስቴር በየደረጃዉ ከሚያደርጋቸው ህብረተሰብ ዓቀፍ ሀገራዊ የተሳትፎና የምክክር መድረኮች ዉስጥ አንዱ ነዉ።